የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚዉሉ ማለትም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽህፈት እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኮምፒተራይዝድ እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያዎች ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣ የቧንቧ እቃዎች እና የወጥ ቤት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በ2018 ዓ.ም የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ነገር ግን የኤሌክትሪክ የኤሌክትሮኒክስ፣ የኮምፒተራይዝድና ተዛማጅ እቃዎች የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በታች ቢሆንም የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከቀረቡት ዝርዝር መግለጫ ዉጭ የሞላ ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡ ናሙና የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰርት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 99 0000 57 41 622 ደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ብለው በማስገባት እና አድቫይሱን ከሞሉት ሰነድ ጋር አብረው ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለተጠቀሱት ቁሳቁሶች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከላይ በተጠቀሰው አካውንት ቁጥር በመክፈል እና አድቫይሱን ይዞ በመቅረብ ከደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 06 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረም እና የድርጀቱን አድራሻ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም እና ክብ ማህተም በማድረግ ጨረታዉ በግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ተኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 2:30 ድረስ በመስሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ 2፡30 ታሽጎ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ሥርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ፓራፍ መደረግ ያለበት ሲሆን ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ዉጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ ወይም በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ውል በመያዝ ኮሌጁ ድረስ ሙሉ በሙሉ ሲያቀርብ እና በባለሙያ ተረጋግጦ ገቢ ሲሆን ብቻ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉን የሚያወዳድረዉ በሎት ይሆናል፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበዉ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ገዥዉ መሥሪያ ቤት በጨረታ ሰነድ ዉስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በ20 በመቶ የመጨመር ወይም 20 በመቶ የመቀነስ መብቱ የተሰጠበት ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 05 32 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደጀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

