የጨረታ ሰነድ ቁጥር KFW 02/2
በጀርመን መንግስት የልማት ትብብር ባንክ /KfW/ የደቡብ ወሎ ደን ልማት እና ብዝሀ ህይወት ሀብት ጥበቃ ፕሮጀክት ጅፒኤስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በ60.00 /ስልሳ ብር/ በመግዛት ከድርጅቱ በመውሰድ መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የባንክ ሲፒኦ /ቢድ ቦንድ/ በማስያዝ በፖስታ በማሸግ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው የሥራ ቀናት ዉስጥ ግዥ ቢሮ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በጨረታ መዝጊያው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3:30 በድርጅቱ ግዥ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ከ20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ለሆኑ ግዥዎች ቫቱን በግማሽ በመቶ ቢሮው የሚያስቀር መሆኑን አናሳውቃለን፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት በነጠላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 62 06 ወይም 09 18 18 73 68 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን
ባ/ዳር