ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት እና ጽህፈት መሳሪያዎችን እና የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች (ግለሰቦች) የሚከተሉትን መስፋርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ክሪላንስ የሚያቀርቡ፣ የታደስ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋው ላይ 2 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚችሉ ሆኖ አሸናፊው ከተለየና ውል ከተያዘ በኋላ ያልተመረጡ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ስነዱን ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ባ/ዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮወርጊስ ቤተክርሲቲያን አጠገብ ከሚገኘው ቢሮአችን ሰነዱን በመግዛት ዝርዝር መረጃውን ማግኝት ይችላሉ፡፡
  4. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ጨምሮ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ስነድ ላይ ስምና ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን ማሰፈርና የድርጅቱን ማህተም በትክክል ያረፈበት ሆኖ በፖስታ በማሸግ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ዋጋው ታክስን ጨምሮ በትክክል ተሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡
  7. ጨረታው የሚገመገመው በተናጠል በሚቀርብ ዋጋ ይሆናል፡፡
  8. የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በሰልክ ቁጥር 058 320 70 44 /058 220 88 91 ደውሎ ወይም ባ/ዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮወርጊስ ቤተክርሲቲያን አጠገብ ከሚገኘው ቢሮአችን በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here