ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
14

በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለሰ/አቸ/ወ/መ/ት/ ጽ/ቤት ከይስማላ- ጨሊያ ላለው የመንገድ ጥሪጊያ ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚዉሉ 1ኛ ግሬደር (cat) ፣2ኛ.ዶዘር (cat) ፣3ኛ.ሎደር (cat)፣4ኛ. ገልባጭ መኪና (ባለ16 ሜ.ኪዩፕ) ፣5ኛ.ሮሎ (ባለ14 ቶን) እና ሻወር ትራክ (ቦቴ) ያላቸዉን ጠ/ስ/ ተቋራጭ  እና መንገድ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉን ተቋራጮች ማወዳዳር ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጸን፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የእቃ (አገልግሎት) ግዥውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 50,000 ብር (ሃምሳ ሺ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በጥሬ ገንዘብ በመሂ /1 ከሰ/አቸ/ወ/ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት  ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው  ቀን  11፡30 ድረስ ተሽጦ በ22ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከተቻለ የንግድ ስራ ፍቃዳቸውን የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሰ/አቸ/ወ/ግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ 05 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው በቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ በሎት ወይም በምድቡ ውስጥ የሚገኙትን እቃዎች የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ እንዲሁም የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፤ ካልጻፉ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ከሰ/አቸ/ወ/ግ/ን/አስ/ ቡድን ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  12. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ከ20በመቶ ቀንሶም ይሁን ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  14. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ሁሉን የጨረታ ሰነዶች እና ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን  የለበትም ሆኖም ግን ስርዝ  ካለው ፊትለፊት ፓራፍ  ወይም መፈረም ይኖርበታል ፡፡ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ ፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. ሌሎች በማስታወቂያው ያልተካተቱ ጉዳዩች በግዥ አፈጻጸም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡

የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here