የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ለመሰብሰቢያ አገልግሎት የሚውል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ደረጃ 7 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 6 ህንጻ ሥራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ደረጃቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በማሰራት ዋጋ ከሞሉት የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት (bill of quantity) በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት ከገንዘብ ያዥ ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/አ/ትብ/መምሪያ በ3፡30 ታሽጉ በ4፡00 ይከፈታል እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም ከኢንሹራንስ የሚሰጥ ዋስትና በምዕ/ጎጃም/ዞ/ገንዘብ መምሪያ ስም ማስያዝ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

