የአዴት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ /ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ እቃዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የተኝቶ ታካሚ የምግብ አቅርቦት፣ የተሽከርካሪ እና የጀኔነተር እቃዎች፣ እና መለዋወጫ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የካፍቴሪያ የምግብና የትኩስ መጠጦች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የክፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የፅህፈት መሳሪያዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሰፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 40 (አርባ ብር) ብቻ በመክፈል አዴት ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ የስ/ ሂደት ከገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢን ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጫራታ ሃሳቡን በአንድ ፖስታ ዋና ወይም ኦርጅናል በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዴት ሆስፒታል በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 20/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 4/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በቀን ጥር 5/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን ማለትም የፅህፈት መሳሪያዎችን አዴት ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ድርጅት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 5554555 ደውለው ማግኘት ይችላሉ ወይም ቢሮ ቁጥር 39 በአካል ቀርበው ማናገር ይችላሉ፡፡
የአዴት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

