የጨረታ መለያ ቁጥር 04/2018
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ የሚያሰራውን የደም ባንክ ግንባታ ሥራ በGC እና BC በደረጃ 5 እና በላይ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር አያይዘው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የፋይናንሻል እና የቴክኒካል በተለያየ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ወርክ ሜትዶሎጅ እና ወርክ እስኬጁል ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጨረታው ሲሞላ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መሞላት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ በወጣው በግልጽ ጨረታ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ዋና እና ቅጅ በማድረግ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ ጥር 12/2018 ዓ.ም 3፡30 ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 1የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዱን በእን/ከ/አስ/ከተማ/መ/ል/ጽ/ቤት ግዥፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለደም ባንክ ግንባታ ለሎት 1 ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ የተጋነነ ዋጋ ዝቅተኛ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ያስይዛል፡፡ ውል በሚይዝበት ወቅት በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚሰራውን ከላይ የተገለፀውን ፕሮጀክቶች (ሥራዎች) ማንኛውንም ማቴሪያሎች ወጭ በራሱ አቅርቦ መስራት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ቅድመ ክፍያ የሚወስድ ከሆነ እስከ 30 በመቶ የሚከፈል ሆኖ ለዚህ ቅድመ ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችል፡፡ አከፋፈሉም በቴክኒካል ግምገማ መስፈርቱ በተቀመጠው መሰረት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የውድድሩ ሁኔታ በሎት ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የውል ማስከበሪያው ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 60 (ስልሳ) ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማ/መ/ል/ጽ/ቤት ግዥፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 00 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

