የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የጣና ክፍለ ከተማ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን የ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት ፣ የጽዳትና አላቂ እና ቋሚ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
- የጽህፈትና የጽዳት እቃ ግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከኦርጅናል ጋር በማመሳከር ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጽህፈትና የጽዳት የአገልግሎት ግዥውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጽህፈት፤ የጽዳት አላቂ ቋሚ እቃዎች አገልግሎት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 5,000.00 (አምስት ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ )ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ጣ/ክ/ከ/ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 ብር 100 ብር በመክፈል መዉሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ዓይነት በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም በዋናና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ድምር ነዉ፡፡
- መመዘኛውን አሟልታችሁ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ20/04/2018 ዓ/ም እስከ 04/05/2018 ዓ/ም በጣና ክፍለ ከተማ ግዥ/ፋይ/ንብ አስ/ቡድን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታውን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
- ጨረታው በ1ኛው ቀን ማለትም በ5/05/2018ዓ/ም ከጧቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጣ/ክ/ከ/አስ/ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 84 በመደወል ዝርዝር ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ባህር ዳር ከ/አስ/ የጣና ክፍለ ከተማ ግ/ፋ/ን/አ/ቡ

