ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
148

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች በክልሉ ውስጥ በሚገኙ  ፍርድ ቤቶች ማለትም በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ በጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ በኮምፖልቻ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤትና በፎገራ ወረዳ ፍርድ ቤት ለምቹ ችሎቶች አገልግሎት የሚውሉ  ሲሲቲቪ ካሜራ፣ ኤን ቪ አር፣  ቴሌቪዥን፣ ሣዉንድ ሲስተም በስፔስፊኬሽኑ መሰረት በማሟላትና በፍርድ ቤቶች ላይ በአካል ተገኝተው በመገጣጠም እንዲሁም ለፍርድ ቤት የአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 56 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቢሮው ቢሮ ቁጥር 50 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከመጋቢት 16/2016 እስከ መጋቢት 30/2016 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ሚያዚያ 01/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 50 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 50 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 82 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here