ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ዓመታዊ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣የኤሌክትሮኒክ እቃዎች፣የፈርኒቸር እቃዎች፣የውሃና የኮንስትራክሽን እና የሙዚቃ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሚሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና አግባብ ያለው የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብርከፋይመለያቁጥር /ቲን/ ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ይህንን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድመቶብር/ ብቻ በመክፈል በሙሉዓለም ባህል ማዕከል ቢሮ ቁጥር 05 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት 4:30 ይከፈታል፡፡ ቀጣዩ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሕዝባዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ከኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ከተፈቀደላቸው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም ከሁኔታዎች ጋር ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ለገ/ያዥ በመክፈል የደረሰኙን ኮፒ ከመወዳደሪያ ዶክመንቱ ጋር አያይዘው ማቅረብይ ኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በ2 ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባትአለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታው በተገለጸ ከ5 ቀናት በኋላ አሸናፊው ድርጅት ላይ ቅሬታ ካልቀረበ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከተጠየቀው ስፔስፊኬሽን ውጭ የሚያቀርብ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሁሉንም መሞላት ያለባቸውን የጨረታ ሰነዶችን መሙላትአለባቸው፡፡ የሚመረጡት በእያንዳነዱ በየሎቱ ድምር መሰረት ዝቅተኛ ዋጋ ይመረጣል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- መስሪያቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው መጠን 20በመቶ ዝቅ ወይም ከፍ ማድረግ ይችላል፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲሁም ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በማግኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-226-53-42 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ማሳሰቢያ፡-በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ላይ ከተጠቀሰው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ውጭ መሰረዝና መደለዝ የራሱን ስፔስፊኬሽን የሞላ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ ሌለበት ሰነድ የሚያቀርብ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
ሙሉዓለም የባህል ማዕከል