ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
22

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ. በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች  ወደ ደ/ታቦር፣ ነፋስ ወውጫ እና ወረታ ከተማ 1ኛ. 20,000 (ሃያ ሽህ) ኩ/ል  የተለያየ ሰብል፣ 2ኛ. 12,000 (አስራ ሁለት ሽህ) ኩ/ል የኢንዱስትሪ ምርቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ቢያንስ 200 ኩ/ል እና በላይ መጫን የሚችል መኪና ያላቸዉ እና የመኪናዉን የሊብሬ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የአገልግሎት ግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ተወዳዳሪዎች ማወቅ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያጓጉዙበትን ቦታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎሕ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ከፍሎ በመግዛት ሰነዱ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ታሽጎ 8፡40 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ሆኖም 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ  ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ዋጋ ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዉ በተለየ በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርበታል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ለማጓጓዝ ከተረከበ በኋላ ካሸነፈበት የዩኒየኑ ማዕከል /መጋዝን/ ድረስ ሳይጎድል፣ ሳይበላሽ እና ሳይጠፋ የንብረቱን ደህንነት ጠብቆ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
  11. የመጫረቻ ዋጋዉ ዉል ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ወራት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  12. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀ/ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የሚጓጓዘው ሰብልና የኢንዱስትሪ ምርት መጠን ከላይ ከተገለጸው ሊጨምርና ሊቀንስ ይችላል፡፡

ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here