ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
21

በምዕ/ጐጃም/ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የተለያዩ  ጨረታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሎት1. ሶፍትዌሮችን ጅፒኤስ ግዥ ፣ሎት2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ ሎት3. የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ ዕቃውች ግዥ፣ ሎት4. የተለያዩ አልባሳት ግዥ፣ ሎት5. ህትመት ግዥ ፣ሎት6. የአትክልት ዘር ቀይ ስርና ካሮት ሽያጭ፣ ሎት7. የፋብሪካ  መለዋወጫ  እቃዎች ግዥ፣ ሎት8. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ሎት9 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ግዥ፣ ሎት10.  የሰብል መደርደሪያ ፓሌት ግዥ ብዛት 100፣ ሎት11. መጋረጃ ቁሳቁስ ከነእጁ እና ምንጣፍ ግዥ ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ሎት 12. የዱቄት ፋብሪካ ሙሉ ሰርቢስ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ወይም ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ሁለት በመቶ ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ወይም በጥሬ ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታው ዋጋ ከ000 (ሁለት መቶ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ጫረታ የቫት ግብይት ከሆነ ከነቫቱ መሆን አለበት፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቀረቢያ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፓስታው ውስጥ ማስገባት እና ፓስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ከላይ በተገለፀው አግባብ የመጫረቻ ሠነዳቸውን በማዘጋጀት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሁሉም ሎቶች ለ7 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆንና ዘወትር እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆን እና ጨረታው በሰባተኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በሚቀጥለው ቀን በ8ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  10. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  11. አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገበ ስልክ ቁጥር 058 774 640/ 1032 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
  15. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  16. የንብረቱ ማስረከቢያ ቦታ ከዩኔኑ ፅ/ቤት ድረስ ነው፡፡

በምዕ/ጐጃም/ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here