ቁጥር ግዥ022/07/18
በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ የማስተማሪያና የቢሮ እቃዎችን ማለትም የእስቴሸነሪ፣ የኮንስትራክሽን፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የኮፒውተርና የኤሌክትርክ ሲቲ፣ የፈርኒቸር፣ ሞባይል፣ የብርታብረት፣ የጋርመንት ፣የቤት እቃወች እና የቢሮ ማስዋቢያወች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ በመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ የእሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለስራ የተዘጋጀውን ሰነድ ዘወትር በስራ ስዓት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በመ/ኢ/ፖ/ቴ/ኮ/ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር4 በ150 ብር መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ በ16ኛ ቀን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን የፖስታ ሳጥኑ 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡30 ተወካዩቻቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊው ይለያል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ሶስት በመቶ በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ የክፋያ ትዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ከአሸነፉ በኋላ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ ሲፔኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን ማስገባት አለባችሁ፡፡
- አሸናፊው እቃዎቹን ኮሌጁ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- ውድድሩ የሚለየው በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና ማህተማቸውን በማስፈረም ዋናውን እና ቅጁን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃው ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 54 55 30 ወይም 0918330604 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የመካነ ኢየሱስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

