ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
23

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ልዩ ልዩ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒከስ፣ ሎት 5 ህትመት እንዲሁም ሎት 6 የመኪና ጎማ በሎት ተዘርዝሮ የቀረበ ሲሆን የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ  መሰረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1-4 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመከፈል ከግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 32 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕ/ጎ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 32 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከታህሳስ 20/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 04/2018 ዓ/ም ድረስ ከቀኑ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጥር 05/2018 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምዕ/ጎን/ዞን/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ሂደት ውስጥ በግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 32 ጥር 05/08 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው አሸናፊ የሆነው አካል ንብረቱን የሚያስረከበውና ውል የሚወስደው በምዕ/ጎ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 32 ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 058 331 07 58 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here