ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
18

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥና ፋይናንስ አስ/የሥ/ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንፅህና መጠበቂያዎች እና የፅህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቀረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ሓይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ግዥና ፋ/ ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጀት ግፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታዉ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከሞቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ይከፈታል፡፡  የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. የንጽህና መጠበቂያ እና የጽህፈት መሳሪያ አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
  10. የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች አሸናፊው የሚለየዉ በተናጠል ዋጋ ነዉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ከጨረታዉ ዉድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠዉን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
  12. ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  13. ሁሉም የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡
  14. አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎቹን ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን አስረክቦ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በክፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 10 65 ወይም 033 222 04 83 ደዉሎ መጠየቅ ይችላል፡፡

የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here