በአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ በደቡብ ወሎ ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ የወረኢሉ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፤ ለኮሌጁ አገልገሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ሎት1.የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2 .የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት3.የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት4. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5. የሆቴል ቱሪዝም ማሰልጠኛዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የገዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽሀ) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ዝርዝር ጨረታው የሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ለአንድ ሎት በመክፈል ከኮሌጁ ገንዘብ ያዥ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውን በመጥቀስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሎት ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላበት ቦታ ካለ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በቀጣዩ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ማሸጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ አቅርቦት ላይ ውል ከመወሰዱ በፊት 20 በመቶ በጀቱ እየተጣመመ የሚጨመር ወይም የሚቀነስ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በወረኢሉ ፖ/ቴ/ኮ በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 03 31 16 02 50/03 31 16 04 85 መደወል ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ተጫራቾች መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና እና ስፔስፊኬሽን መሰረት የተጠየቁትን እቃዎች ማቅረብ
ይኖርባቸዋል::
የወረኢሉ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

