የቢቡኝ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የእንስሳት መድሀኒት፣ ሎት 3 የፎቶ ግራፍ እና እይታ መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የንፅህና ዕቃዎች፣ ሎት 5 ክሎሪን፣ ሎት 6 የቅድመ መደበኛ ት/ቤት ግንባታ፣ ሎት 7 የቢቡኝ ገነተ ማርያም ቀበሌ የአ/አድር ማሰልጠኛ ግንባታ፣ ሎት 8 የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ፣ ሎት 1፣ 3፣ 4 በድጋሜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
- በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለመድሀኒት ግዥው የሙያ ፈቃድ ወይም ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ለግንባታው የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የእቃውን ዝርዝር እና የግንባታ ሥራ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሎት 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5 ብር 100 (አንድ መቶ ብር) እና ሎት 6፣ 7፣ 8 ብር 500 (አምስት መቶ ብር) የማይመለስ ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋለሎት 1 ብር 20,000፣ ለሎት 2 ብር 10,000፣ ለሎት 3 ብር 10,000፣ ለሎት 4 ብር 1,000፣ ለሎት 5 ብር 2,000፣ ለሎት 6 ብር 100,000፣ ለሎት 7 ብር 20,000፣ ለሎት 8 ብር 40,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በስራ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የዕቃ ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ16 ተኛዉ ቀን ጥር 5/2018 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ለግንባታ ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ22 ተኛዉ ቀን ጥር 22/2018 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለዕቃ በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለበት ፊት ለፊቱ መፈረም አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
- ለግንባታ ጨረታው በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም
- በ2014 በጀት ዓመት ተሻሽሎ የወጣውን የግንባታ መመሪያ ተግባራዊ ይሆናል)
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 00 47 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ፍርድ ቤት

