በአብክመ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር የሰቆጣ ማረሚያ ቤት መምሪያ ለማረሚያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽ/መሳሪያና ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ የስልጠና እቃ፣ የግንባታ እቃዎችን እና ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የወጣ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከ100,000 (ከመቶ ሺ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልፅ በሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላሉ ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ጀምሮ ከ20/4/2018 እስከ 4/5/2018 ከጥዋቱ 3፡00 ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ፖስታ ውስጥ አብረው እንዲያሽጉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ፤በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 14 61 23 11 እና በስልክ ቁጥር 09 92 04 68 95 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የሰቆጣ ማረሚያ ቤት

