በቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኝ ሴ/መስሪ ቤቶች በ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ለይቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክ፣ ሎት 3 የውሃ እቃ፣ ሎት 4 የቢሮ አጥር ግንባታ፣ ሎት 5 የአሶል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ስለሆነም የሚመለከታቹህ ተጫራቾች ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚፈለገውን እቃ አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊክሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና በመሂ 1 የተቆረጠ ጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ከታህሳስ 20/2018 እስከ ጥር 04/2018 ዓ.ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጥር 05/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋራ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ጥር 05/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የመክፈቻ ቀን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ጥር 05/ 2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክ ጥር 05/2018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 3 የውሃ እቃ ጥር 06/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 4 የቢሮ አጥር ግንባታ ጥር 12/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 5 የአሶል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ጥር 12/02018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ቋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስከረብ አለበት፡፡
- እቃውን የምንረከበው በያዝነው የበጀት ልክ ነው፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ነው፡፡
- ከላይ ደረጃ 9 ተብሎ የተገለፀው ለቢሮ አጥር ግንባታ እና ለአሶል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የግንባታ ጨረታዉ 21 ቀን ሚዉል ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ወይም ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 271 02 69 /00 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

