በሰሜን ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካባቢ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ውስጥ ለሴክተር መ/ቤቶች 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ AM /mreawi /UIIDP/G/01/2025/06፣ ሎት 1 ጀነሬተር ግዥ AM mreawi /UIIDP/Go JDF/02/2025/2026፣ ሎት 1 ፈርኒቸር AM mreawi /UIIDP/Go/03/2025/2026፣ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ AM mreawi /UIIDP/Go/04/2025/2026 እንዲሁም የጽዳት ዕቃዎችን /UIIDP/Go/05 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሆነ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አይይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ፖስታ በማሸግና በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥር በማስፈር በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀቡ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መርዓ ከ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ብር 17,734 (አሰራሰባት ሽህ ሰባት መቶ ሰላሳ አራት ብር)፣ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ 4,797 (አራት ሽህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ብር)፣ ሎት 1 ፈኒቸር 8,090 (ስምንት ሽህ ዘጠና ብር) ሎት 1 የጽዳት ዕቃዎችን 330 (ሶስት መቶ ሰላሳ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ባለሙያ ማየት የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በባለሙያ ታይተው ገቢ የሚደረጉ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ክተገለጸ በኋላ የድርጅቱን ስም የሚጠቅስና ተከታታይ ቁጥር ያለዉ ህጋዊ ደረሰኝ በማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚያቀርበውን የእቃ አይነትና ጥራት ናሙና ቀድሞ የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይና በ16 ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 የሚከፈትና አሽናፊ የሚለይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈትለት ቀን የህዝብ በዓል ቀንና የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበትም ሆነ በሌሉበት ሠነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በመ/ቤቱ የተሻለ ጥቅም አገኛለሁ ብሎ ካመነ አሸናራውን በተናጠል ዋጋ ወይም በጠቅላላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛቸው ዕቃዎች ላይ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያዉ ላይ ያልተጠቀሰ ነገር ቢኖር በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተፈጻሚ ያሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ መርዓዊ ከ/አስተዳደር ገንዘበና አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካባቢ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

