ፀደይ ባንክ (አ.ማ) ቻግኒ ቅርንጫፍ ለአቶ ተዋቸው አምበሉ እና ወ/ሮ ጥሩነሽ ብርሃን ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በሰንጠረዥ ከዚህ በታች የተገለጸ መኖሪያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦኞች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪ ስም | የካርታ ቁጥር/የይዞታው መለያ ቁጥር | ቤቱ የሚገኝ በት ቦታ | የቦታው ስፋት | የንብረቱ አይነትና አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀንና ሰአት | ጨረታ የወጣው |
| ተዋቸው አምበሉ እና ጥሩነሽ ብርሁኑ | ተዋቸው አምበሉ እና ጥሩነሽ ብርሁኑ
|
7163/11 | ቻግኒ 04 ቀበሌ | 250 ካ/ሜ | ለመኖሪያ | 2,414,622.35 | 28/05/2018 ዓ/ም ከ4፡00-6፡00 | ለመጃመሪያ ጊዜ |
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃላ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመከሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ከሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሽናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፈል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 እና 091 8 74 55 34 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ዲስትሪክት

