ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
113

(ቁጥር 01/17)

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ልጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሚሰሩ ተፋሰስ ሥራዎችን ሎት 1 ከሞላ ይመር ቤት እስከ ሙሀመድ አስፋዉ ቤት፣ ሎት 2 ከሙሀመድ አስፋዉ እስከ ያሲን ቤት፣ ሎት 3 ከያሲን ቤት እስከ ከድጃ ቤት ድረስ አዲስ ተፋሰስ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የግብር ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
  4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ደረጃ 9(ዘጠኝ) እና በላይ የሙያ ፈቃድ ያላቸው (ደረጃ 10 አያካትትም)
  6. የሚጫረቱበት ጨረታ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት በመቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 79,000.00፣ ሎት 2 90,000.00 ሎት 3 97,000.00 በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋጋ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. የሥራዉን ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳብን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመርሳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 09/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/04/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በ31ኛው ቀን በ10/04/2016 ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም 09 13 28 23 42 /09 35 21 25 15 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የአሸነፋቱን ሎት የማቴሪያልና የጉልበት ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ነዉ፡፡
  16. ሥርዝ፣ ድልዝ እና ፍሉድ መጠቀም አይቻልም፡፡ ከጨረታ ዉጭ ያደርጋል፡፡
  17. የጨረታ ዋጋ ጸንቶ መቆያ ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀን የጸና ይሆናል፡፡
  18. ሶስት እና ከዚያ በላይ ተወዳዳሪዎች ከቀረቡ አርቴሚቴክ ዉጤት ልዩነት ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ በላይ ከመጣ ተቀባይነት የለዉም ከ3 በታች ተወዳዳሪዎች ከቀረቡ ከ አንድ በመቶ በላይ የአርቲሜቲክ ልዩነት ተቀባይነት የለዉም፡፡

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here