ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
52

የፍኖተ ሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም ሎት1∙ ጅኤስ ቧንቧን መገጣጠሚያ፣ ሎት2∙ ኤች ዲፒ መገጣጠሚያ ሎት3∙የቧንቧና መፍቻዎችና የስራ መሳሪያዎች፣ ሎት4∙ ሲአይ መገጣጠሚያ፣ ዲሲአይ መገጣጠሚያና  ቆጣሪ፣ ሎት5∙ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት6∙ የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት7∙ የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት8∙ ኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ሎት9∙ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት10∙ የዉሃ ጥራት ኬሚካል ሪኤጀንት፣ ሎት 11∙ እስቴሽነሪ፣ ሎት12∙ የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት13∙ ኤክስትራክተር፣ ሎት14∙ ኩሽኔታ በግልጽ  ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1.  በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ከብር  200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ለሆነ ተጨማሪ  እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
  4. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም በዉሃ አገልግሎቱ  ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከ1-5 የተዘረዘሩትን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ::
  6. የጨረታ ማስታወቂያዉ ማስታወቂያ  በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታትሞ ይዉላል፡፡  በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ  ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን  በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር አራት  በተዘጋጀዉ  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ::
  8. ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም::
  9. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል  ከሆነ በሚቀጥለዉ  የስራ ቀን  በተመሳሳይ  ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለሳል፡፡
  11. ተጫራቾች የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ::
  12. አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ  ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት  ዉስጥ ያሸነፉበትን የሎት ዕቃዎች ጠ/ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (በጥሬ ገንዘብ) ለፍኖተ ሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍ/ሠ/ከ/ዉ/ፍ/አገ/ ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ ፡፡
  13. ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ ወይም ሎት በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ::
  14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ ድርጅቱ ኃላፊነትን አይወስድም::

ለበለጠ መረጃ  በስ/ቁ 058 77 51 387 /00 75/09 23 42 61 23 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

የፍኖተሠላም ከ/ዉ/ ፍ/ አገ/ ድርጅት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here