ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
61

በአብክመ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እቃዎችን ሎት1∙ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት2.የፅዳት እቃዎች፣ ሎት3.ህትመት፣ ሎት4. ቋሚ እና አላቂ እቃዎች፣ ሎት5. የኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 6. የፈርኒቸር፣ ሎት7∙ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡመሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙት የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፌክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከተጠቀሰው ስፔስፌኬሽን ውጭ ሰርዞ ሌላ ስፔስፌኬሽን መቀየር ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያውን ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም በሚወጣው ጋዜጣ መመልከት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምሪያ በሎጅ /ፋይ/አስ/ዋ/ ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 ብር 20 (ሀያ) ብር በመክፈል ከግዥ ባለሙያዋን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር (በጥቅል) ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመሂ1 በመቁረጥ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አይቻልም። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች   ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታ መ/ቤታችን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በሰሜን ጎንደር ዞን ፖ/መምሪያ በሎጅ/ፋይ/አስ/ዋ ክፍል በስራ ሰዓት ማስገባት እንደሚችሉ እንገልፃለን በማለት በጥንቃቄ ታሸጎ ቢሮ ቁጥር 8 ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጸንቶ የሚቆየው ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 11/05/2018 ዓ/ም ድረስ የሚቆጠር15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል።
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰ/ጎን/ፖ/መምሪያ በሎጅ/ፋይ/አስ/ዋ/ ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 ጥር 12/2018 ዓ.ም ከጧቱ በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል።
  12. አሸናፊዎች እቃዎችን የሚያስረክበት በሰ/ጎ/ ፖሊስ መምሪያ በሎጅ/ፋይ/አስ/ዋ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 ይሆናል፡፡
  13. የግዥ መጠኑ ከ20,000 (ሃያ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ ተጫራቹ 3 በመቶ ታክስ መክፈል አለበት።
  14. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ የጨረታ አሸናፊው የሚለውየው በሎት ወይም በነጠላ በሞላው ዋጋ ሲሆን ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው። ያልሞላ ተጫራች ቢኖር ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  16. አሸናፊው ተጫራች የእቃዎችን ጥራት በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጥራቱን በማረጋገጥ ማስረከብ ግዴታው ነው፡፡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ መሰረት የጥራት ችግር ያለባቸውን ሙሉ በሙሉ በመመለስ ትክክለኛ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። የርክክቡ ቦታ ደባርቅ በሰ/ጎን/ዞን ፖሊስ መምሪያ በሎጅ/ፋይ/አስ/ ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 ይሆናል።
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች በስልክ ቁጥር 09 18 15 16 54 ወይም 09 18 73 23 59 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here