ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

የቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2  የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 4 ኤሌክትሪካል እቃዎች፣ ሎት 5 የቧንቧ እቃዎች፣ ሎት 6 ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች እንዲሁም ሎት 7 ፈርኒቸር በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች  ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያለቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ተጫራቾች የሚመለከታቸው ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ በመግለጽና በፖስታ በማሸግ የድርጅታቸውን ማህተም በማስፈር ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 68 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸዉን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ15 ተኛው ቀን  11፡00 ድረስ ተሸጦ በዚያኑ ቀን 11፡30 ታሽጉ በ16ተኛው ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ከረፋዱ በ3፡30 ላይ ይከፈታል፡፡  ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እህድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ ከጨረታው አሸናፊው ላይ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን ይገለፃል፡፡
  10. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና እራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
  11. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት (ምድብ) ውስጥ የሚገኙትን እቃዎች የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልተፃፈ ግን የተሞሉትን ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  12. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. መ/ቤቱ እንደአስፋላጊነቱ 20 በመቶ ቀንሶ ወይም ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ማንኛውንም ወጪ ሸፍነው ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በአፈፃፀም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  17. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 68 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 665 04 83 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here