በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ውስጥ ወርክሾፕ አዳራሽ በመደበኛ ካፒታል በጀት በሙሉ ዋጋ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚጠገኑትን ግንባታዎች የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጥገና ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 27/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 13/2018 ዓ/ም ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ነገር ግን ጥር 11 እና 12 ተከታታይ አመታዊ በዓል በመሆኑ ምክንያት ለ17 ቀን እንዲቆይ ሁኗል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅ ፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከላዊ ጎንደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከታህሳስ 27/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 13/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሆነ ባይገኙም ጨረታዉ በሰዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ጥር 13/2018 ዓ/ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ቁጥር 09 64 79 28 60 ወይም 09 18 73 44 61 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

