ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

በሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የአንጎት ወረዳ ፍ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚሰጡ ማለትም፡- ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የእጅ መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የሚሰሩ እና የሚገጣጠሙ ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 ማሽነሪዎች/የኤሌክትሮኒክስ/ እቃዎች፣ ሎት 7 የደንብ ልብ ብትን ጨርቆች እና ሎት 7 የተዘጋጁ የደንብ ልብትሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁና /ቲን/ ያላችሁ፡፡
  2. የምትሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱ አርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማንኛዉም ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡
  4. ከሞላችሁት እቃ ድምር አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቅድሚያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ተጫራቾች ለክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/ 2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
  7. የጨረታውን ሰነድ ከ9/03/2017 እስከ 24/3/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/ወ/ፍ/ቤት በቀን 24/3/2017 ዓ/ም በ 3፡30 ታሽጎ የሚከፈተው በ4፡00 ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ያሸነፉቸውን እቃዎች አ/ወ/ፍ/ቤት አሁን ተገኝ ከተማ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይገባቸዋል፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፍ/ቤቱ ሥልክ ቁጥር 21 97 57 90 /09 48 85 84 27 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአንጎት ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here