ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
139

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ ላሉ ተቋማት የቢሮ ግንባታ ለወረዳዉ ፍትህ ጽ/ቤት እና ፍርድ ቤት G+2 ደረጃ 5 ሙያ ፈቃድ ያላቸዉ፣ ዉሃ ጽ/ቤት ማህበራትና እንስሳት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ ደረጃ 6 ሙያ ፈቃድ ያላቸዉ የጋማዉበርና አፀደማርያም ቀበሌ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል FIC ግንባታ ደረጃ 6 የሙያ ፈቃድ የላቸዉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና የሙያ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ብቻ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይንት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የግንባታዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከገንዘብ ያዥች ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የግንባታዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራቾች ጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ጥር 27/2018 ዓ.ም በ3፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 270 05 97 /195 /194 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here