ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
28

በድጋሚ የወጣ የኦዲት (የሂሣብ ምርመራ)

የወልድያ ከተማ ውሃ አገ/ት (ድርጅት) የ1 ዓመት ማለትም የ2017 ዓ.ም  በጀት ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች በጋዜጣ አወዳድሮ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን  መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. መ/ቤቱን (ድርጅቱን) ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱ፡፡
  3. በሂሣብ ምርመራው (ኦዲት) ተግባር ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድ ወዘተ … ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተያዘ (የተገባ) የቅጥር ውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የበጀት ዓመት ሂሣብ ኦዲት ለማድረግ በተሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ሁለት በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያከናውኑትን ተግባር በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡
  6. ተጫራቾች ስለ መልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድርጀቶች የተፃፈላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት (ተመዝጋቢ ከሆነ)፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (ቲን ) እና ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
  8. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) ወልድያ ከተማ ውሃ አገ/ት መ/ቤት (ድርጅት) ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፉ፡፡
  9. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ) ብር በመግዛት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዓመት ኦዲት ሥራ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትን የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር (ማስኬጃ ውል) በማዘጋጀት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. የጨረታው ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጧቱ በ3፡00 ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ  በዚሁ ቀን በ 3፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 3 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 033 43 107 99፣ 03 34 31 12 23 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. Email gechmog@gmail.com ፋክስ

የወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት መ/ቤት (ድርጅት)

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here