በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በመቅደላ ወረዳ የማሻ ከተማ መሪ ማዘጋጃ በ2018 በጀት አመት የሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ የገረጋንቲ መንገድ ስራ ለማሰራት የማሽን ኪራይ 1. ዳምፕትራክ (ገልባጭ መኪና ሲኖ ትራክ) ጎማቸው አዲስ የሆነ በጠቅላላ 16 ሜትር ክዩብ መያዝ ያለበት ሲሆን ከሚሰራበት ሳይት በአማካይ 6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ማቴሪያል የመጫን ሰራ ማቅረብ ያለበት የሲኖ ብዛት ከ6 (ስድስት) በላይ መሆን አለበት፡፡ የቢያጆ ብዛት 700፣ 2. ሞተር ግሬደር የስራው ሰአት 160 (አንድ መቶ ስልሳ) ሰአት፣ 3. ቫይብሬተር ሮለር 14 ቶን በላይ ክብደት ያለው የስራው ሰአት 120 (አንድ መቶ ሀያ) ሰአት፣ 4. የውሀ ቦቲ 18000 ሊትር የሚይዘ (አስራ ስምንት ሺ ሊትር) መሆን አለበት ቢያጆ 20 የሆነ፣ 5. ኢክስከቫተር ከነ ጃክሀመሩ እግሩ የሰንሰለት የሆነ 305 (ሶስት መቶ አምስት) እና በላይ መሆን አለበት የስራው ሰአት 250 (ሁለት መቶ ሀምሳ) ሰአት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ማሽኖች 2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረቱ ምርቶችን ማቅረብ የሚችሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ለ2018 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው 2017 ዓ.ም የስራ ግብር ክፍያ የከፈሉ፡፡
- የጨረታ መጠን ወይም የግዥ መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)
- ክፍያ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም እቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ወይም 25 በመቶ ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነጻ ገበያ ላይ ተመስረቶ መሆን አለበት፡፡
- የተጫራቾች የአንድ ማሽን ሙሉ የስራ ወጭ ዋጋ እና የጠቅላላ ማሽን የሥራ ወጭ ዋጋ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ተጫራቹ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለማሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ለሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁት በአማረኛ ቋንቋ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቦታ ደ/ወሎ ዞን መቅዳላ ወረዳ የማሻ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከ 04/05/2018 እስከ 24/05/2018 11፡00 ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት የመትችሉ ይሆናል፡፡ በ22ኛዉ ቀን 3፡30 ይዘጋል፡፡ በዚህ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በቀን 25/5/2018 ዓ.ም በይፋ ይከፈታል ነገር ግን በበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታን ለማደናቀፍና የጨረታ ጊዜን ለማጓተት የሚሞክር ተጫራች በግዥ መመሪያው መሰረት ህጋዊ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 09 08 88 00 92/ 09 14 54 38 72/ 09 42 81 62 11/ 09 46 29 22 53/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማሻ ከተማ መሪ ማዘጋጃ

