ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ የከርሰ ምድር ውሃ በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይዞ ማስቆፈር (ማሰራት) ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የዘርፉ ተጫራቾች መወዳደር  ትችላላችሁ፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የሥራ ደረጃቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 25 በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሥራ ደረጃቸው ከደረጃ 1-6 መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. በሥራው ከዚህ በፊት ከሚሞሉበት የሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ መ/ቤታችንም የምስክር ወረቀቱ ትክክለኛነቱን በቀጥታ የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ2 ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም፣ የድርጅቱ ማህተም፣ አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጥር 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ጨረታው በ22ኛው ቀን ማለትም ጥር 25/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. ሥራው የሚያስፈልገው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  14. አሸናፊው በውሉ መሰረትና በወጣው የመሃንዲስ የሥራ ዝርዝር መሰረት ሰርቶ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
  16. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  17. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  18. መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላይ ከተጠቀሱት የስራ ዝርዝር ላይ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሰራት መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
  19. መ/ቤቱ አሽናፊውን የሚለየው በጥቅል ድምር ዋጋ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ሁሉም በጨረታው የተቀመጡትን የሥራ ዝርዝር ዋጋ ሙሉ ለሙሉ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 22 05 04 /09 18 21 06 28 /09 23 22 10 87 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here