የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም፡- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ፣ ሎት 2. የእህል ምርት ውጤቶች (ዛላ በርበሬና ቅመማ ቅመም)፣ ሎት 3. አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲሁም ሎት 4. የኮምፒተር መሳሪያዎችና ተጓዳኝ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኙት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ ከት/ቤቱ ገ/ያዥ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነበር፣ የቫት የምስክር ወረቀት የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጥር 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም ጥር 19/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው ) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ መኖር የለበትም፡፡ ነገር ግን ሥርዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሎት የጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን ምርቱን (እቃውን) በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኙ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
- አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

