የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የውሃ ጥራት ሪኤጀንት እቃች፣ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎችን፣ የጽሕፈትና የጽዳት መገልገያ እቃዎች እና Desk top Computer በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ሎት 1. የውሃ ጥራት ሪኤጀንት እቃዎች፣ ሎት 2. የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ሎት 3- የጽሕፈትና የጽዳት መገልገያ እቃዎች እንዲሁም ሎት 4. Desk top Computer ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (የታደሰ) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናሉን ኮፒውን እና ሲፒኦ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (un Conditional Bank Garanty) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 05 83 20 50 79 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

