ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በሙያዉ የተሰማሩ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የሚሳተፉ ተጫራቾች የእቃውን ወይም አገልግሎቱ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፣ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. የሚገዙ እቃዎች አገልግሎቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 33 የጨረታ ሰነዱን ማግኘትና ማየት ይቻላል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ብቻ ) በመክፈል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመክፈል ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስታወቂው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይ/ንብ/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥራ አስተዳደር ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 1068 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 2030 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የአብከመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here