የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለሥራ የሚፈልጋቸውን ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች እና ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬት (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 27 ከጥር 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 18/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ጥር 19/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ን/የስራ ሂደት ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 14) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል (ቴክኒካልና ፋይናንሻል እና አንድ ኮፒ ቴክኒካልና ፋይናንሻል) የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥር 19/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ በአገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 የሥራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የሥራ ቀን ይቆጠራል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 33 16 /058 112 06 97 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

