ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
48

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግክ/ ቡድን በ2018 በጀት አመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የማንጎ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እና የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የማንጎ ዘሩ 60 (ስልሳ) ኩ.ል ሁኖ በዛፉ ላይ በጣም የበሰለ ወደ ቢጫነት የተቀየረ ከበሽታና ተባይ ነጻ የሆነ፣ ያልተላጠ እና ግብዓቱ ሲቀርብ ከኳራንታይን ጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቹ ሙሉ ስም አድራሻ ፊርማ ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ስነዶቻቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ከቢ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት/ደ/ሃ/ደ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ጽ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥር 4/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 18/2018 ዓ.ም 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 10:30 ላይ ይታሸጋል፡፡
  8. ጨረታዉን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግቢ/ዕ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ጥር 19/2018 ዓ.ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸበት ከ05 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 05 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን 20 በመቶ የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን በዓል ፣ እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ግብዓቱ የሚቀርበው በሙሉ ወይን ዉሃ ችግኝ ጣቢያ ሲሆን በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 06 04 /09 10 62 76 34 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here