የጎንደር ከተ/ወረ/ፍርድ ቤት ግዠና ፋይናንስ ንብረት አስተዳዳር ቡድን በመ/ቤቱ ላሉ የስራ ሂደቶች ፤ ለአዘዞና ጠዳ ንኡስ ወረዳ ፍ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ሎት 1.የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. ከጥጥ የተሰራ ካፖርት ሸሚዝፕ፣ የዝናብ ልብስና ጥላ ፣ ሎት 3.የሀገር ውስጥ የሴትና የወንድ አጭር ቆዳ ጫማና ፕላስቲክ ቦት ጫማ ፣ ሎት 4. የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም አላቂ እቃዎች ፣ ሎት 5.የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 7. የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ፣ሎት 8. የህትመት ውጤቶችና ቲተሮች፣ ሎት 9. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ ግዥዎችን የሚከተሉትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በየሎቱ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት አያይዘው የሚያቀርቡ፤ከ200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ለሚያቀርቡ ጠቅላላ ዋጋ ድምር እና ለኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች ደግሞ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ከሎት1. እስከ ሎት 9 የማይመለስ 00 /ሀያ ብር/ በመክፈል ጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ የሚቆየው ከህዳር 9 /2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም ድረስ ይሆናል፡፡ ህዳር 24 /2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግዥና ፋይናንስ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
- የሚገዙ አቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ከሞሉት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም ሲፒኦ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤቱ ግዥ እና ፋይናንስ ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ከገንዘብ ያዥ በመ/ሂ 1 ለማስያዛቸው የገቢ ደረሰኝ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ 2 ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 እስከ ህዳር 24/2017 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃውን መጓጓዠ እና ማንኛውንም የመንግስት ታክስ ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መ/ቤቱ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፍትን እቃ ጎን/ከ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- የሚጠገኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤የሚጠገኑ እቃዎች የሚጠገኑበት ቦታ በማእከላዊ ጎን/ከ/ወ/ፍ በመ/ቤቱ ላሉ የስራ ሂደቶች እና ለአዘዞና ጠዳ ንኡስ ወ/ፍ/ቤቶች ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጎንደር ከ/ወ/ፍ ቤት የግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስ/ቡ/ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 00 36 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ /ወ/ፍርድ ቤት