በምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የሰከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለሰከላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች ለተለያየ አገልግሎቶች የሚውሉ ማለትም ሎት 1. የዘገዝ ወንዝ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል (ፕሮቴክሽን ዋል ስራ በአብክመ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያና አደጋ መከላከል ኮሚሽን በአውሮፓ ዩኒየን በጀት ድጋፍ፣ ሎት 2. የግሽ-ዓባይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የአጸደ ህጻናት መማሪያ ክፍል ግንባታ በክልል ድጎማ በጀት፣ ሎት 3. FTC (የአርሶ አርደሮች ማሰልጠኛ ቢሮ ግንባታ) በመደበኛ ካፒታል በጀት ደረጃ 7 እና በላይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ፣ ሎት 4. ስሚንቶ፣ ሎት 5. ፈርኒቸር እና ሎት 6. ክሎሪን በመደበኛ በጀት ሎት 1 እና 2 ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እንዲሁም ሌሎች ሎቶች በዘርፉ ፈቃድ ያላቸዉን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የግንባታ ፈቃድ እና ለእቃዎች በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም ለግንባታዎች የመልካም ሥራ አፈጻጽም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩትን ማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫራቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል፡፡ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለያንዳንዱ ሎት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለግንባታዎች እና ለአቃዎች ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእቃዎች እስከ 15 ቀናት ለግንባታዎች ደግሞ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ሰከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ዘወትር በስራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት የዋጋ መጠን ሎት 1 እና 2 ለያንዳንዱ ሎት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና የሎት 3 ብር 60,000 (ስልሳ ሽህ ብር) ለእቃዎች ደግሞ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሽህ ብር) ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ ደረሰኝ ማረጋገጫ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ክመጫራቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ በሠከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለግንባታዎች 21 ቀናት ለእቃዎች 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ የሚከፈተዉ ለግንባታዎች በ22ኛዉ ቀን ለእቃዎች 16ኛዉ ቀን እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ ብቻ የመጫረቻ ሠነዳቸውን በተዘጋጀው የመጫረቻ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሠከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዉ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ 10 በመቶ በሠከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ያሸነፈበትን የግንባታ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፤ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ የጨረታ አሸናፊዉ በወጣዉ ጨረታ ዝርዝር መሰረት አገልግሎትን በተገቢዉ ሁኔታ እያስኬደ ካልሆነና ከመነሻዉ ጀምሮ አሰራሮችን ካጓተተ የሚያቀርበዉን ቅሬታ የማንቀበል መሆኑ ታውቆ ለሚደርስበት ኪሳራም መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- በጨረታ ዘርዝሩ የተገለጹትን አስተካክሎ መሙላት፣ ሥርዝ ድልዝ እና ነጠላ ዋጋ ያልሞላ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወይም ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ ሠከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ስልክ ቁጥር 058 259 00 09 መደወል ይችላሉ፡፡
የሰከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

