በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአዲስ አለም ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ 07 አይነት ግዥዎችን ሎት1. አውት ሶርስ የላውንደሪ እጥበት አገልግሎት፣ ሎት2. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት3. የመኪና ሰርቪስ የእጅ ዋጋ፣ ሎት4. የተለያዩ የመኪና እስፔር ፓርት እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና የወንበር ልብስ ፣ ሎት5. የተለያዩ የደንብ ልብስ ስፊት፣ ሎት 6. የአልትራሳውንድ CBC ማሽን እና ማይክሮስኮፕ ማሽን፣ ሎት 07 የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
- ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያየዘው ማቅረብ አለባቸው፤ በዚህ ያልተጠቀሱ የጨረታ መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተጨማሪ የሚቀርቡትን የመገምግሚያ ነጥቦች ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የላውንደሪ እጥበት አገልግሎት የስራ ልምድ ከመንግስታዊ ድርጅት የሁለት አመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ የሰሩበት የምስክር ወረቀት ወይም የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል፡፡
- በሎት የወጡት 7ቱም የጨረታ አይነቶች እና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩ ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን 10በመቶ የውል ማስያዣ ያስይዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ ሆስፒታል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
አዲስ ዓለም ሆስፒታል
ባህርዳር

