ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

በደቡብ ጎንደር ዞን የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀትና በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ እቃዎችን 1. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 3. የጽዳት እቃዎች፣ 4.የህንጻ መሳሪያ እቃዎች፣ 5. የስፖርት ማሰልጠኛ እቃዎች፣ 6. የቧንቧ ውሃ እቃዎች፣ 7. የተሸከርካሪ መለዋዎጫ እቃዎች፣ 8. የኤሌክትሪክ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. ተወዳዳሪዎች የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ )ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡
  4. ኮሌጁ ከብር 20,000 (ሃያ ሽህ) ብር በላይ ግዥ ሲፈጽም መንግስት በሰጠው ውክልና መሰረት 7.5 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
  5. ኮሌጁ ከብር 20,000 (ሃያ ሽህ) ብር በላይ ግዥ ሲፈጽም ሶስት በመቶ የዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
  6. በሰነዱ ላይ የተጠቀሰዉ ቁጥር ብዛት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  7. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  8. የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር  በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም  በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒዉን ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  11. ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ተገልጾላቸው ያሸነፉትን የዕቃ ጠቃላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ዋናዉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 16 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 4፡30  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡35  ይከፈታል፡፡
  14. ዉድድሩ በተናጠል የምናወዳድር መሆኑን ተወዳዳሪዎች ሊያዉቁት ይገባል፡፡
  15. አሸናፊዎች እቃዎቹን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ንብረት ክፍል ገቢ በማድረግ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 14 100 31 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  18. ተጫራቶች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  19. አድራሻ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደ/ታቦር ከተማ በጌምድር መ/ራን ትም/ ኮሌጅ ነው፡፡
  20. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 141 00 31 መደወል ይችላሉ፡፡

የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here