ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
79

የጨረታ ቁጥር፡- የጨረታ ቁጥር EPSS/10/2018

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባሕር ዳር ቅርጫፍ የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ የግንባታ ሥራ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአገልግሎት መ/ቤታችን በማግኘት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በየኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቦርድ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከታህሳስ 27/2018 እስከ ጥር 18/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ጥር 19/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡10 ባሕር ዳር ከተማ ጣና ሀይቅ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮአችን ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአገልግሎታችን በአካል በመቅረብ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የግንባታ ሥራ የጠቅላላውን ዋጋ ብር 2 በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  6. ይህ ጨረታ በአገልግሎት መ/ቤታችን የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  7. የጨረታዉ አሸናፊ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  8. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን:- 058 226 51 52

የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት

 ባ/ዳር ቅርንጫፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here