ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ ኢ/ት/መምሪያ የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 5 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 6 ብትን ጨርቅ እንዲሁም ሎት 7 የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን መስፈርት የሚሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመሰስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/መ/ገ/ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ ከጥር 11/2018 እስከ ጥር 25/2018 ዓ/ም ድረስ በመምጣት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደረበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ለለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በጠ/ወ/ገ//ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ጥር 26/2018 ዓ.ም 8:00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
  9. በሎት 7 የተጠቀሰው የመኪና መለዋወጫ አቅርቦቱ ጋራጁ በሚገኝበት ጎንደር ከተማ መሆኑን እያሳወቅን ውሉ የአንድ አመት ኩንትራት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  10. ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ድምር በመሆኑ ባዶ ቦታ ዋጋ ሳይሞሉ ማስገባት ከጨረታ ውድቅ ያደርጋል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 71 95 88 80 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here