ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
103

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች  አገልግሎት የሚዉል  የጭነት የመኪና ኪራይ ባህር ዳር ደርሶ መልስ ኦክስጅን ሲሊንደር አስሞልቶ ጭኖ ለማምጣት እና መዳህኒት ከጎንደር ወደ መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማምጣት   በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ መከራየት  ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የመኪናውን ሊቭሪ (የባለቤትነት ማረጋገጫ) ፎቶ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ለጨረታ የሚቀርበው ተሸከርካሪ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት ሚውል መሆኑን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ኦክስጅን ሲሊንደር ያልተሞላውን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ጭኖ ባህርዳር ኦክስጅን ማምረቻ አስሞልቶ መተማ ሆስፒታል ማምጣት የሚችል፡፡
  7. የመድን ኢንሹራንስ ውል ያለው እና ኮፒውን ማስያዝ የሚችል፡፡
  1. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በመተማ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን ከ 09/03/2017 እስከ 23/03/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ 24/03/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለው እና በሰነዱ ላይ ስም እና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 01 74 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጭነት ዋጋ  አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  1. የጭነቱ  አይነት በቢያጆ፡፡
  1. አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ እንዲጫን በሚጠየቅበት ሰዓት በአስቸኳይ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ኦክስጅን ሲሊንደር ከመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ባህር ዳር ጭኖ አስሞልቶ ለማምጣት በሚሄድበት ቀን  በመብራት መጥፋት ምክኒያት ወይም በወረፋ ምክኒያት ቢዘገይ ወረፋውን ጠብቆ አስሞልቶ መምጣት የሚችል  መሆን አለበት፡፡

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here