ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት የፍርን የመጀመሪያ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ GC/BC የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተቋራጮች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ በGC/BC ሥራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴዎች መለያ ቁጥር የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ወቅታዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው አስፈላጊ የምትሏቸውን ሰነዶችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠ/ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. የሞሉት ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የዋጋ መሙያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በተለያዩ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ ትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች አካቶ በማሸግ ፍ/ሠላም ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 43 ፊት ለፊት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ይቆይና በ22ኛው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፍ/ሠላም ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 43 ከዋና ገ/ያዥ እጅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለግንባታው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ይሆናል፡፡
  8. በዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻለም፡፡
  9. ተጫራቸች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልጾላቸው ውል ባለመያዛቸው ወይም በገቡት ውለታ መሠረት በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ሥርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አስቸጋሪ የሆነ የዋጋ አቀራረብ ከጨረታው ውጪ ያስደርጋል፡፡
  12. የጨረታው መክፈቻ ቀን አጋጣሚ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. በዚህ የግዥ ሂደት የሚነሱ አለመግባባቶች ወይም ያልተነሱ ነጥቦች 2003 ዓ.ም በወጣው የግዥ መመሪያ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 43 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 16 29 /883 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here