ሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በኮን ከተማ የሚገኘዉ የኮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለኮሌጁ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ለሆቴል ዲፓርትመንት ቋሚ እቃዎችን፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎች አላቂና ቋም፣ ሎት 5 የጂኤምኤፍ ኤ አላቂ እቃዎች፣ ሎት 6 የbei አላቂና ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 7 የአይሲቲ የት/ርት ቋሚ አላቂ እቃዎች እንዲሁም ሎት 8 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸዉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ የሚቸሉ፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒዉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከጥር 11/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 25/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ስዓት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ (መግዛት) ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 26/2018 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የእያንዳንዱ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በኮን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታዉ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸዉን ከጨረታዉ ማግለል አይቻልም፡፡
- ዉድድሩ የሚካሄደዉ በሎት ድምር ዉጤት ነዉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ መጠን አንድ በመቶ የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና በጥሪ ገንዘብ ማሰያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስም ፊርማ የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸነፊዉ በተጠቀሰዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት ንብረቱን (እቃዉን) ማቅረብ አለበት፡፡ ከተጠቀሰዉ ስፔስፊኬሽን ዉጭ ይዞ ቢቀርብ በሚደረሰዉ ኪሳራ ተቋሙ ተጠያቂ አይሆንም ንብረቱ በባለሙያዉ ተፈትሾ ነዉ ገቢ የሚሆነዉ ጥራት የጎደለዉ እቃ ኮሌጁ ያለመረከብ መብት አለዉ፡፡
- በማንኛዉም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይቻልም፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጨረታዉ አሸናፊ የሆኑና ከተገለጸላቸዉ በአሽነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታዉ አሽናፊ የሆነ ተወዳዳሪ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 5 ተከታታይ ቀን ድረስ በኮሌጁ ቀርቦ ዉለታ መዉሰድ ይኖርበታል የት/ርትና የጭነት ወጭዎች አሸናፊዎች የሚችሉ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- እቃዉን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት በዓል ቀን ከሆነ /ዝግ/ ከሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 85 01 04 /09 63 51 46 01 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

