ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ለትምህርት ሥልጠናና ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጥሬ እቃዎች 1. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 3. የጨርቃ ጨርቅ እቃዎች 4. የጽህፈት መሳሪያ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ ቁጥር (ቲን ) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፍ እግድ ያልተጣለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የቫት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የጨረታው ቦታ ሞጣ ፖ/ቴክ/ ኮሌጅ/ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት እስከ ቀኑ 4፡00 ድረስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ኮሌጁ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  5. ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸውን፣ ቲን ነምበራቸውን ፣ቫት ሪጅስተራቸውን ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታቸው ጋር ኮፒ አድርገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000 (ሁለት ሺህ) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያውን ዋስትና ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ በግልጽ ጽሁፍ በመጻፍና በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፤ ቀርበው ተገቢውን ውል ባይፈጽሙ የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ አድርጎ ኮሌጁ የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
  10. የክፍያ ሁኔታ ውል የያዘባቸው ወይም ግዴታ የገባበትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ በባለሙያ ተረጋግጦ ለኮሌጁ ንብረት ክፍል በራሱ ወጭ እቃዎችን አቅርቦ ገቢ ሲያደርግና ሞዴል 19 ሲያቀርብ ሙሉ በሙሉ ክፍያ ይፈጸምለታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ገንዘብ ያዥ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 058 661 04 32 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ ኮሌጁ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  13. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 661 04 32 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here