ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
57

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ የክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት ለዲች ሥራ የሚውል ስሚንቶ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ያለባቸው፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ቁጥር ያላቸው፡፡
  3. ያቀረቡት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በሲፒኦ በባንክ በክ/ድንጋይ መሪ ማ/ቤት ስም ያስይዛሉ፡፡
  6. ከ1-5 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው ተጫረቾች (ህጋዊ ወኪሎቻው) በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 12 በ15ኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  8. የስሚንቶ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቹን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም እና ጨረታ ያወጣውን መ/ቤት ስም እና አድራሻ በመግለጽ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት ባዘጋጀው ሳጥን ያስገባሉ፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ የአንዱን ኩንታል ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡ የ1 ሰነድ ዋጋ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ነው፡፡
  11. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ክ/ድንጋይ መሪ ማ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  12. ማ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ 09 18 71 44 11 መደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here