ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሚገኘው የጎህ ሁለ/የገበ/ኅ/ስ/ማህበራት ዬኒየን ኃ.የተወሰነ  የእንስሳት ምጥን መኖ ለማምረት አገልግሎት የሚውል ጥሬ ዕቃ 1ኛ. በቆሎ 1,200 ኩንታል፣ 2ኛ. የኑግ ፋጉሎ 600 ኩንታል፣ 3ኛ. የአኩሪ አተር ፋጉሎ 600 ኩንታል፣ 4ኛ. የሱፍ ፋጉሎ 300 ኩንታል ፣ 5ኛ. የስንዴ ፉርሽኪሎ 200 ኩንታል፣ 6ኛ. የምግብ ጨው 30 ኩንታል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 2 በመቶ በባንክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋሰትና) አስይዘው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ የሚያሲዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከዬኒየኑ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእንስሳት ምጥን መኖ ጥሬ እቃ አቅርቦት ዋጋ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖራው የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋውን ሞልተው በፖስታ አሽገው ከዬኒየኑ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በወቅቱ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ዋጋ ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆናል፡፡
  7. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ አስይዞ በ5 ቀን ውስጥ ከዬኒየኑ ቀርቦ ውል መውስድ አለበት፡፡
  9. ተወዳዳሪው ያሸነፈበትን የእንስሳት ምጥን መኖ  ጥሬ ዕቃ  ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን  ድረስ   የንብረቱን ደህንነት ጠብቆ ሳይጎድልና ሳይበላሽ በራሱ ትራንስፖርት አጓጓዞ ማቅረብ ወይም ማስረከብ አለበት፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ጥሬ ዕቃውን ሲያስጭን እና ለዩኒየኑ ንብረት ክፍል ሲስረክብ የማስወረጃ የሰራተኛ የጉልበት ክፍያ ወጭን አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ይሸፍናል፡፡
  11. ዪኒየኑ ያወጣውን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  12. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. አድራሻ ፡- ደ/ታቦር ከተማ ጸደይ ዲስትሪክት ባንክ አንደኛ ፎቅ ነው፡፡

ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here