ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
52

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በሎት 1. የጤና ጣቢያው የመለስተኛ ቀዶ ጥገና ክፍል እና የምርመራ ክፍል ግንባታ ለማስጨረስ ሎት 2. የፊርማሲ ክፍል ማስፋፊያ ግንባታ ለማስገንባት የእጅ ዋጋ እና ማቴሪያልን ጨምሮ ጥቅል ዋጋ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  4. ሁሉም ተጫራች የመልካም ሥራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. በከተማ ልማት የግንባታ ምስክር ወረቀት ከደረጃ 7 እና በላይ ያላቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸውጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከጤና ጣቢያው ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠዳ ጤና ጣቢያ በግዥና ን/ፋን/አስ/ቡድን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ22ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይክፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. የስራዉ ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
  11. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058 448 03 33 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠዳ ጤና ጣቢያ ግ/ፋን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጠዳ ጤና ጣቢያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here