ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
105

በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታል ሥራ አገልግሎት የሚውሉ እነዚህ የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1 የደንብ ልብስ (1.1 ብትን ጨርቃ ጨርቅ ፣ 1.2 የተዘጋጁ ልብሶችና 1.3 ጫማዎች) ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3 ህትመት ሎት 4 የፅዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ካለው ፖስታ ከውጭ ወይም ከውስጥ አያይዘው ማቅረበብ አለባቸው፡፡
  5. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈረትቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የመጫረቻ ሰነድ መግዣ በመክፈል ሸበል በረንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 የእድውሃ ከተማ ድረስ በአካል በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ቀን /ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገፅ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም በማድረግና በፖስታው በማሸግ ሰነዱን በእያንዳንዱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ሸበል በረንታ የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 በተጠቀሰው ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ባገኘም ጨረታውን ከመክፈት የማያስቀረው መሆኑንና በጨረታው ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበት እቃ በራሱ ትራንስፖርት ወጭ የዕድውሃ ከተማ ሸበል በረንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ እቃውን በአይነትና በመጠን ቆጥሮ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
  10. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን አስር በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላያ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ እና ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. ዋጋ ሲሞሉ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መሞላት አለበት፣ ሥርዝ ድልዝ ካለበት ፊርማቸውን ከፊት ለፊት ወይም ከምርመራው ላይ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች በተገለፁት መመሪያ ይዘቶች ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 247 02 39 /294 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሸበል በረንታ የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here